Back

“በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት የደረሰው የአይሮፕላን አደጋ የብዙ ሀገራት ዜጎችን ቢጎዳም ዓለም የበለጠ አስተሳስሯል" ፕሬዝዳንት ማክሮን

ኦቢኤን   መጋቢት 05 2011- የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑዬል ማክሮን ይህን ያሉት በናይሮቢ "አንድ ዓለም" ("One Planet") በሚል ርዕስ በአፍሪካ አህጉር ለመጀመሪያ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ነው።

ፕሬዝዳንት ማክሮን በመክፈቻ ንግግራቸው "ይህ አሳዛኝ አደጋ የዓለም ሀገራትን በዚህ ፈታኝ ወቅት እንደ አንድ ቤተሰብ አንዲቆሙ አድርጓቸዋል" ብለዋል።

በእሳቸው ጠያቂነትም ለተጎጂዎቹ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት የተደረገ ሲሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስትም መፅናናትን ተመኝተዋል።

የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታም በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ቤተሰቦች፥ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።

በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኑዮ ጉቴሬዝ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የድርጅቱ ረዳት ዋና ጸሀፊ አድርገው የድርጅቱ የኬንያ ቢሮ አድርገው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በኬንያ ቆይታቸውም ለስራቸው መቃናት የአገሪቱ ህዝብና መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል።

በዚህ ጉባኤ ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ፥ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር በሆኑት ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ ተወክላለች።ምንጭ፦The Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia