Back

የኢትዮ-ጀርመን የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

OBN ሚያዚያ 07፣2011የኢትዮ-ጀርመን የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተደረገ
ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) እና የባቫሪያን የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ ክልላዊ ልማትና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ሮላንድ ዊገርት ፈርመውታል፡፡

ማዕከሉ የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቴክኖሎጂዎች የሚለሙበትና ወደ ምርት የሚቀየሩበት ነው ተብሏል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የምርምርና የፈጠራ ስራ ያላቸው ወጣቶች ስራዎቻቸውን የሚያዳብሩበት፤ ወደ ምርት የሚቀይሩበትና ገንዘብ እንዲያስገኙ የሚደረግበት ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ ዘርፍ የዳበረ ልምድ ካላቸው ሀገራት ጋር ዘርፉ የስራ እንድል እንዲፈጥር ለማድረግ በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡ መረጃው የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚ/ር ነው፡፡