Back

የኦሮሞና ሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጋራ መድረክ በአዳማ ይካሄዳል፡፡

OBN ሚያዚያ  212011  የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦችን አንድነትንና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ያለመ የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንስ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው እንደገለጹት ኮንፈረንሱ የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦችን ወንድማማችነት በማጠናከር በሰላም፣በልማትና በአገር ግንባታ ውስጥ እያበረከቱ ያሉትን ሚና ለማስቀጠል የታለመ ነው።

በአዳማ ከተማ በሚካሄደው በዚህኮንፈረንስ ሁለቱ ህዝቦች የጋራ አኩሪ እሴቶቻቸውን ለአገራዊ አንድነትና ለውጥ ትርጉም ባለው መልኩ ለመተግበር እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ኪራይ ሰብሳቢ አመራሮችና ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት የወሰን አስተዳደርን እንደ ሽፋን በመጠቀም በፈጠሩት ብጥብጥና ሁከት በሁለቱም ወገን ለሰው ህይወት መጥፋት፣ለንብረት ውድመትና ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።

የክልሎቹ የለውጥ አካላትና የፌዴራል መንግሥት ተባብረው በመስራት ችግሮቻቸውን ማስወገዳቸውንም አቶ አድማሱ አስረድተዋል። ኢዜአ