Back

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከእንግሊዝ ኣቻቸው ጋራ በፅ/ቤታቸው ተወያዩ

OBN ሚያዚያ  242011 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብት በማድረግ ላይ ከሚገኙት ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ጀርሚ ሃንት በጋር ጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሁለቱ ከቡራን ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ እና በክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርገው ተወያይተዋል።

ክቡር አቶ ገዱ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በለውጥና በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ላይ የምትገኝ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህ ረገድ እንግሊዝ ለሀገሪቱ  እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍም አመስግነዋል።

የአካባቢው ሰላም ከኢትዮጵያ ሰላም ጋር በእጅጉ የተቆራኘ በመሆኑ በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በስፋት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች ብለዋል ::

ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደት እንዲመሰረት ኢትዮጵያ ከአካባቢው አገሮች ጋር በቅርበትና በትብብር እየሰራች ትገኛለችም ብለዋል።

የእንግሊዝ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እያደረጉ ያለውን የኢቨስትመንት እንቅስቃሴ አድንቀዋል። እንግሊዝ በአገራችን በንግድ እና በኢንቨስትመንት ያላትን ጉልህ ድርሻ አጠናክራ እንደምትቀጥል ሙሉ እምነታቸው መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ጀርሚ ሃንት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እየወሰደች ያለውን ቆራጥ የሪፎርም ሂደት አድንቀዋል። ለዚህም እንግሊዝ ሙሉ ድጋፏን ትሰጣለች ብለዋል ፡፡

 

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እውን እንዲሆን እንግሊዝ የዲሞክራሲ ተቋማትን አቅም በማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ በአካባቢው ሰላም እንዲስፍን እያደረገች ያለውን ሰፊ ስራም እንግሊዝ ታደንቃለች ብለዋል።

 

 እንግሊዝ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍንም ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

የእንግሊዝ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የእንግሊዝ መንግስት ለባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍም ያደርጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ለዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው። ሁለቱ አገሮች በኢኮኖሚ፣ በዲፐሎማሲ እና በባህል ዘርፍ ጥብቅ የሆነ ግንኙነት አላቸው።