Back

የመጀመሪያው ብሄራዊ የማህበራዊ ዋስትና ጉባኤ በፊንፊኔ እየተካሄደ ነው

OBN ግንቦት 052011  ጉባኤው በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ የማህበራዊ ዋስትናን ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሚኒስትሯ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ያለ አካታችና ሁሉን አቀፍ ልማት ማሳካት እንደማይቻልም ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በጋራ መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር የሆኑት ቶርቦርን ፒተርሰን በኢትዮጵያ እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦችን አድንቀዋል።

ጉባኤው "ማህበራዊ ዋስትና ለአካታች ልማት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።