Back

ትዊተር 125 ሺህ አድራሻዎችን አገደ

ጥር 30፣2008

ትዊተር ከ125 ሺህ በላይ ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዙ አድራሻዎችን ከአውሮፓያኑ 2015 አጋማሽ ጀምሮ ማገዱን አስታወቀ፡፡

በዓለም ከ500 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት የማህበራዊ ትስስር ድረገፅ ትዊተር በተለይም ከአሸባሪው የአይኤስ ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸውን አድራሻዎችን ነው ያገደው፡፡

የማህበራዊ ትስስር ድረገፁን በመጠቀም ሽብርተኝነትን የሚደግፉትን እንደሚያወግዝና በአድራሻዎቹ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ትዊተር በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡       

በአሜሪካ የሚገኘው ትዊተር ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤት ማምጣት መጀመሩንና እንደ አስፈላጊነቱም ከህግ አስከባሪ ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

የአለም መንግስታት አመፅን ለማነሳሳትና ሽብርተኝነትን ለማስተዋወቅ ድረገፆችን የሚጠቀሙ አካላት ላይ ህብረተሰቡ የማህበራዊ ትስስር ድረገፆችን በመጠቀም እንዲያወግዛቸው ሲጥሩ ቆይተዋል፡፡   

የአውሮፓ ህብረትና የአሜሪካ መንግስታት እንደ ትዊተርና ፌስቡክ ያሉት የማህበራዊ ትስስር ድረገፆች ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ በጋራ ለመስራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

ምንጭ፡- ቢቢሲ