Back

ሁለተኛው የአፍሪካ ዙርካን የባህል ስፖርት ውድድር ተጀመረ

ታህሳስ 05/2008

ሁለተኛው የአፍሪካ ዙርካን የባህል ስፖርት ውድድር ትናንት ታህሳስ 04/2008 ዓ.ም ተጀመረ፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተገኝተው ውድድሩን ያስጀመሩት የኢ.ፌ.ድ.ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አንበሳው እንየው ኢትዮጵያ ውድድሩን ያዘጋጀችው የኦሎምፒክ ስፖርቶች የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ካላት ከፍተኛ ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡