Back

የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ጉባኤ መሪዎችን በመምረጥ ተጠናቀቀ

ታህሳስ 23፣2008

የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን 16ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ መስፍን አበራን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም ሌሎች 6 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በመምረጥ ተጠናቀቀ፡፡

ጉባኤው በ2007 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2008 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ተወያይቷል፡፡ ፡፡
በውይይቱ የፕሪሜር ሊግ ክለቦች የውድድር ተሳትፎ መጨመር፣ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች ለሚገኙ የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ሰልጣኞች ድጋፍ መደረጉ እንዲሁም ከአለምአቀፉ  የቮሊቦል ፌዴሬሽን ጋር ጠንካራ ግንኙነት መፈጠሩ በጥንካሬ የታዩ ሆነዋል፡፡

የውስጥ ገቢ በበቂ ሁኔታ መሰብሰብ አለመቻሉ፣ ችግር ፈቺ የሆነ ጥናታዊ ፅሑፍ አለመጠናቱ ፣ ለክልል ፌዴሬሽኖች እና ለታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ስልጠና በተጠናከረ መልኩ ድጋፍ አለመደረጉ በሪፖርቱ በድክመት ከተመላከቱት መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ጉባኤውም በቀረበው ሪፖርት ላይ በቀጣይ ቢስተካከሉ ያላቸውን ሀሳቦች በማንሳት ሪፖርቱን አፅድቋል ፡፡

ፌዴሬሽኑን ለ4 ዓመት የሚመሩ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትም በጉባኤው ተመርጠዋል፡፡

አቶ መስፍን አበራን ፕሬዝዳንት ሆነው ሲመረጡ፣ ወ/ሮ ሂሩት መብራቱ፣ አቶ ገበያው እሸቴ ፣ አቶ አስጨናቂ ለማ፣ አቶ ጌታቸው ተሻገር፣ አቶ ብሩክ እሸቱና አቶ ጋሻው ጃኔን በአባልነት ተመርጠዋል፡፡

ምንጭ፡- የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር