Back

ካፍ መስከረም ታደሰን የሴቶች እግርኳስ ልማት ኃላፊ አድረጎ ሾመ፡፡

OBN ጥቅምት 29፣2011    ወ/ሪት መስከረም ታደሰ የካፍ የሴቶች እግር ኳስ ልማት ኃላፊ በመሆን መሾማቸው ተነገረ፡፡

ወ/ሪት መስከረም ዛሬ በካይሮ ግብፅ ካፍ በሚያደርገው ስብሰባ በይፋ ኃላፊነታቸውን እንደሚረከቡ ይጠበቃል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፀሀፊ በመሆን በመስራት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን በቡድን መሪነት በመምራት እንዲሁም የሴካፋ የሴቶች ቻምፒዮና ላይም በፀሀፊነት እና በአስተባባሪነት አገልግለዋል፡፡

ካፍ የሴቶች እግር ኳስ ልማት ኃላፊነትን እንዲመሩ የሾማቸው በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ የሴቶች እግር ኳስ እንዲያድግ ካበረከቱት አስተዋፅዖ አንፃር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወ/ሪት መስከረም ከሹመታቸው በኋላ በሰጡት አስተያየት ከካፍ ጋር በተለይም በሴቶች እግርኳስ ዙሪያ መስራት የሁል ጊዜ ህልሜ ነበር ይህ በመሳካቱም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም  በተለያዩ የካፍ መድረኮች በትጋት የሰሯቸው ስራዎች ለሹመት እንዳበቃቸው ጠቅሰው ከዚህ በኋላም ሁሌም ለመሻሻል እና ይበልጥ ለመስራት እጥራለው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ምንጭ፦ሶከር ኢትዮጵያ