Back

ቻይናውያን የረዥም እና መካከለኛ እርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች በኢትዮጵያ ልምምድ ጀመሩ

OBN ታህሳስ  24፣2011 ቻይና የረዥም እና መካከለኛ እርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶቿን ለቶክዮው ኦሊምፒክ ለማዘጋጀት በኢትዮጵያ እንዲለማመዱ ልካለች፡፡

የቻይና አትሌቶች ቡድን በኢትዮጵያዊው የአትሌቶክስ አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎ ነው የሚመራው፡፡

የቻይና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኢትዮጵያዊውን አሰልጣኝ ሀጂ አዲሎን እስከ የ2020 ቶክዮ ኦሊምፕክ ድረስ በአሰልጣኝነት መቅጠሩ ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የቻይና አትሌቶች ቡድን ከትናንት ጀምሮ በሰንዳፋ ልምምድ መጀመራቸውን ኤሊት ስፖርትስ ማናጅመንት ኢንተርናሽናል ግሩፕ ዘግቧል ሲል አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ በድረ ገጹ አስፍሯል፡፡