Back

በአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና አለሚቱ ታሪኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አሸነፈች

 

OBN ሚያዚያ 08፣2011  ትላንት ምሽት በኮትዲቯር በተጀመረው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲከስ ሻምፒዮና ከ20 ዓመት በታች በ3 ሺ ሜትር የፍፃሜ ውደድር አለሚቱ ታሪኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አሸነፈች፡፡

በርቀቱ አትሌት ፀሀይ ሃይሉ የነሐስ ሜዳሊያ ማስመዝገብ ችላለች።

ከ18 ዓመት በታች በስሉስ ዝላይ ሰንበቴ ሮቢ የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ አስገኝታለች፡፡

ከ20 ዓመት በታች የስሉስ ዝላይ አጁሉ አዱላ 5ኛ ሆና አጠናቃለች።

በወንዶች በ1500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይሁን ፋንታሁን የብር ሜዳሊያ አስመዝግቧል።

በ10ሺ ሜትር ውድድር ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያዉያን አትሌቶች ድል አልቀናቸዉም፡፡ ኬንያ የወርቅና የነሐስ ሜዳሊያ ስታገኝ ዩጋንዳ የሁለተኝነት ደረጃን ይዛለች። በኢትዮጵያ በኩል ደረጀ አዱኛ 4ኛ እንዲሁም ቢተው አደመ አምስተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል። ምንጭ፡- የኢ.አ.ፌ.