Back

የ2022 የወጣቶች የበጋ ኦሎምፒክ ውድድርን አፍሪካ ለማስታናገድ ተመረጠች

[OBN  29- 01-2011]    የአውሮፓዊያኑን 2022 የወጣቶች የበጋ የኦሎምፒክ ውድድርን ሴኔጋል ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ እንድታስተናግድ መመረጧን የአለም የኦሎምፒክ ኮሚቴ ገልጿል፡፡ የኦሎምፒክ ውድድሩም በዳካር፣ ዴምኔዶና ሳሊ በሚባሉ ሶስት የሴኔጋል ከተሞች ላይ እንደሚካሄድም ተመልክቷል፡፡ሴኔጋል በአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተመረጠችው በአርጀንቲና እየተካሄደ ካለው የዘንድሮው የበጋ የወጣቶች ኦሎምፒክ ጎን ለጎን በተካሄደ መድረክ ከቦትስዋና፣ናይጀሪያና ቱኒዝያ ጋር ተፎካክራ ነው፡፡ ለአብነትም ግብጽ በአውሮፓዊያኑ 1936 እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ በአውረፓዊያኑ 2004 የተካሄዱትን የኦሎምፒክ ውድድሮች ለማስተናገድ ቢሞክሩም አልተሳካላቸው ተብሏል፡፡ ሴኔጋል የ2022 የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድርን ለማስተናገድ በአለም የኦሎምፒክ ኮሚቴ ተመራጭ የሆነችው ተፎካካሪዎቿን ቦትስዋና፣ ናይጄሪያና ቱኒዚያን በመብለጥ እንደሆነም ተጠቁመዋል፡፡ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር እድሜያቸው ከ14 እስከ 18 ባሉ ወጣቶች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄድ ነው፡፡  ምንጭ፦ ቲም ዩኤስኤ